Projects
የድርጅቱ የፕሮጀክት አፈጻጸም
1 የምዕራፍ አንድ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራዎችና ስኬቶች
1.1 በፕሮጀክት አጀማመር ወቅት የተሄዱባቸው አሰራሮች
I. ፕሮጀክቱን መተግበር ያስፈለገበት ምክንያት (ለፕሮጀክት መነሻ የሆኑ ምክንያቶች)
የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከአልኮል መጠጥ አምራቾች ዘርፍ ውስጥ የሚገኝ የመጀመሪያ አንጋፋ የአልኮል መጠጥና የአልኮል አምራች ድርጅት ሲሆን፣ምርቱን ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚ ኅብረተሰብና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ መሆኑ ይታወቃል:: ይሁን እንጂ ፋብሪካው ለረዥም ጊዜ አገልግሎት የሰጠና የያዛቸውም የማምረቻ መሳሪያዎች ያረጁና ኋላቀር በመሆናቸው የገበያውን ፍላጎት ማርካት ካለመቻሉም ባሻገር በኤክስፖርት ገበያ ገብቶ ለመወዳደር እንዳይችል አድርጎታል፡፡
About NALF Project