National Alcohol & Liquor Factory

አስደሳች ዜና

አስደሳች ዜና

THE BIZZ AWARDS

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆነውና 15 ዓመታት በላይ የድርጅቶችን አፈጻጸም በተለያየ መለኪያዎች በመመዘን እውቅና በመስጠት በሚታወቀውና 130 ዓለም ሀገራት በመስራት ላይ በሚገኘው እንዲሁም 3500 በላይ ታዋቂ አለም አቀፍ አምራች ድርጅቶች አባል ባሉት WORLD CONFIDERATION OF BUSINESSES, A winner of the most important business excellence award in the world, THE BIZZ AWARDS አሸናፊ መሆኑን ለድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ በድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጄሱስ ሞራን .. ነሐሴ 29/2022 በፃፈው ደብዳቤ በማሳወቁ የተሰማንን ከፍተኛ ደስታ እየገለጽን ይህም የድርጅታችን ሥራ አመራር ቦርድ፤ሥራ አመራርና የመላው ሠራተኛ ጠንካራ አመራር እና ቅንጅት ውጤት ነው፡፡


ይህ ውጤት የተገኘው ድርጅታችን በሥራ አመራር ጥራት ፤የተቀናጀ የአሰራር ሥርዓቶች ትግበራ፤በምርት ጥራት እንዲሁም በትርፋማነትና ውጤማነት ውስጥ ባሉ ዝርዝር መስፈርቶች መሰረት ያለበት የአፈፃፀም ደረጃ ተለክቶ የተገኘ በመሆኑ አሁንም በድጋሚ እንኳን ደስ አለን እያልን በቀጣይም ድርጅታችንን ከዚህ የበለጠ አፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደምናደርሰው ያለንን ሙሉ እምነት እንገልፃለን፡፡

ጥራት መለያችን ነው!!!

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

 363 total views,  4 views today

Contact Us

Mexico Square Behind Addis Ababa Technical College & Mekanissa
info@nalf.com.et, national.alcohol@gmail.com
+251 115 516 999 / +251 115 516 190
+251 115 513 299

Our Location