National Alcohol & Liquor Factory

ዜና ብሔራዊ

ዜና ብሔራዊ

 

ዜና ብሔራዊ

የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የ2015 ዓመታዊ አጠቃላይ የኦፕሬሽን ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ የድርጅቱ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ተወካይ አቶ ሽመልስ ሐብተወልድ ፤የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣የሥራ አመራር አባላትና መላው ሠራተኞች በተገኙበት መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መሥሪያ ቤት በማከናወን ዓመታዊ የሠራተኞች በዓልን በደመቀ ሁኔታ ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም አክብሮ ውሏል፡፡

የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ የ2015 በጀት ዓመት አጠቃላይ የምርት፤የሽያጭ እንዲሁም የኮርፖሬት ሪፎርም መርሃ ግብር አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የማህበራዊ ኃላፊነት የመወጣት ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን የጠቀሱት አቶ መሥፍን አባተ በተጠቀሰው በጀት ዓመት ለሀገራዊ ጥሪ የተደረገውን ድጋፍ ጨምሮ ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አብራርተዋል፡፡ በቀረበው የ2015 በጀት ዓመታዊ አፈፃፀም ሪፖርት መሠረት ከሁሉም የአፈፃፀም መለኪያ መስፈርቶች አኳያ ከመቶ ፐርሰንት በላይ የዕቅድ ክንውን በማስመዝገብ አሁንም ጠንካራ ስኬታማነቱን ማስቀጠል በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ ይህም የሥራ አመራር ቦርዱ፤የሥራ አመራሩና የመላው ሠራተኛ ጠንካራ የተቀናጀ ሥራ ውጤትና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ድጋፍ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ተወካይ ክቡር አቶ ሽመልስ ሐብተወልድ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የህግ ማስከበሪያ ክፍል ኃላፊ በበኩላቸው የድርጅቱ ሥራ አመራር አባላትና ሠራተኞች በቅንጅትና በትጋት በመስራት በዚህ ተለዋዋጭና የተለያዩ ተግዳሮቶች በበዙበት አካባቢያዊ ሁኔታ የድርጅቱን ቀጣይነት ያለው ስኬት እንዲረጋገጥ ማድረጋቸው ምን ያህል የሰለጠነ ሥራ አመራርና ጠንካራ አሰራር ሥርዓት እንዲሁም የኔነት ስሜት ያለው ትጉህ ሠራተኛ እንዳለ የሚያመለክትና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ፅኑ እምነት በመግለፅ ለቀጣዩ የ2016 በጀት ዓመት ስኬታማ ውጤት ለማስመዝገብ ለችግሮች ባለመሸነፍና በጋራ መስራት አስፈላጊ እንደሆነ የሥራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን ለዚህም እንደቀድሞው ሁሉ የሥራ አመራር ቦርዱ ጠንካራ ድጋፍ እንደማይለይ በማረጋገጥ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በቀጣዩ ፕሮግራምም ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካን በምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚነት በቁርጠኝነትና በትጋት አገልግለው በጡረታ ለተገለሉት ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሲመሩና ሲያስፈጽሙ ለነበሩት የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ አማኑዔል ኃይሌ እና ኢንጂነር ምንይበል አየለ እውቅና እና ሰርተፍኬት በዕለቱ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ተወካይ አቶ ሽመልስ ሐብተወልድ አማካኝነት በማበርከት በመጨረሻም የሠራተኞች የምሳ ግብዣና መዝናኛ ፕሮግራም ተከናውኖ ዝግጅቱ ተጠናቅቋል፡፡

ጥራት መለያችን ነው!!

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

 537 total views,  2 views today

Contact Us

Mexico Square Behind Addis Ababa Technical College & Mekanissa
info@nalf.com.et, national.alcohol@gmail.com
+251 115 516 999 / +251 115 516 190
+251 115 513 299

Our Location