ዓለም አቀፍ ዕውቅና!!
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በአለም በ130 ሀገራት በሚገኙ ከ3500 በላይ ድርጅቶችን በያዘውና ዓለም አቀፍ ዕውቅና በመስጠት በሚታወቀው WORLDCOB የ2022 የBIZZ AWARD ተሸላሚ መሆኑን መግለፃችን ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት ይህንኑ ከፍተኛ ሽልማት WORLDCOB እ.ኤ.አ ከኖቬምበር 11-12/2022 በአሜሪካ ሂውስተን ቴክሳስ ከተማ ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ እና ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ በመገኘት ተቀብለዋል፡፡ በወቅቱም የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ የ2022 WORLD LEADER BUISNESS PERSON የተሰኘውን የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ጥራት መለያችን ነው!!
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
508 total views, 2 views today