የገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀው ባለ 12 ነጥብ መመዘኛ ተለክተው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 200 ከፍተኛ ግብር ከፋዮች መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተሰናዳ መርሐ ግብር ላይ የዕውቅና የዋንጫ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ድርጅታችን የተቀመጡትን መስፈርቶች ሁሉ በማሟላት ከልማት ድርጅቶች እንዲሁም ከሌሎች የቢዝነስ ተቋማት ጋር በመወዳደር የወርቅ ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን በመብቃቱ ደስ ብሎናል፡፡
በመሆኑም በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ ድርጅታችን የወርቅ ደረጃ ዋንጫ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እጅ ዋና ሥ/አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መስፍን አባተ ተረክበዋል፡፡ በዚህም የተሰማንን ከፍተኛ የደስታ ስሜት እየገለፅን ለቀጣይ ዓመታትም ይህንኑ በማስቀጠል ድርጅታችንን የምናስጠራበት እና ከአጋሮቻችን ጋር በመተባበር የበለጠ ለመሥራት እንደምንችል በሙሉ ልብ በመተማመን ነው፡፡
2,421 total views, 3 views today