ዓለም አቀፍ ቀኖችን ማክበር!!!
የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የዕለቱን መርሃ-ግብር በይፋ ካስጀመሩ በኃላ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩትን የዓለም ኤድስ ቀን ( መሪ ቃል፡-አገልግሎታችንን ለተጠቃሚዎች በእኩልነት በማድረስ ወረርሽኙን እንግታ!!) ፤18ኛው ዓለም አቀፍ የሙስና መከላከል ቀን ( መሪ ቃል፡- በሥነ-ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ!! ) ፤ ዓለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀን ( ሠላም ይስፈን በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም!! ) በድርጅታችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ጥር 16/2014 ዓ.ም ሠራተኞች አክብረዋል፡፡ በዚህም ወቅት የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች የተከናወኑ ሲሆን በምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ- ሥነ-ምግባርን በተመለከተ፤በሥርዓት ፆታ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ስማችው ሥርዓተ-ፆታንና ፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ እንዲሁም የኤች.አይ.ቪ ኤድስ በሽታ ባህሪያትና መከላከያ መንገዶችን በተመለከተ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ጤና ቢሮ ከፍተኛ ጤና ባለሙያ በአቶ ስንታየሁ ግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም የድርጅታችን የ2014 ዓ.ም መጀመሪያ ስድስት ወራት አጠቃላይ የኦፕሬሽን ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተከናውኗል፡
647 total views, 1 views today