National Alcohol & Liquor Factory

ዓለም አቀፍ ዕውቅና!!

ዓለም አቀፍ ዕውቅና!!

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በአለም 130 ሀገራት በሚገኙ 3500 በላይ ድርጅቶችን በያዘውና ዓለም አቀፍ ዕውቅና በመስጠት በሚታወቀው WORLDCOB 2022 BIZZ AWARD ተሸላሚ መሆኑን መግለፃችን ይታወቃል፡፡

  በዚህም መሰረት ይህንኑ ከፍተኛ ሽልማት WORLDCOB .. ከኖቬምበር 11-12/2022 በአሜሪካ ሂውስተን ቴክሳስ ከተማ ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ እና ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ / ኮከቤ ቁምቢ በመገኘት ተቀብለዋል፡፡ በወቅቱም የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ 2022 WORLD LEADER BUISNESS PERSON የተሰኘውን የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ጥራት መለያችን ነው!!

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

 292 total views,  2 views today

ዜና – ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን መሳተፍ

ዜና

  በአሜሪካን ሀገር ዋሽግንተን ዲሲ በሚገኘው የአሜሪካ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮ-ፕሮሞሽን ኤል.ኤል.ሲ፤ከሄሌዝ ኤቨንትስ እና ከኢትዮጵያ ዘርፍ ማህበራት ንግድ ምክር ቤት ጋር በጋራ በመተባበር የተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የምግብ፤የመጠጥና የባህል ፌስቲቫል መስከረም ከ14-15 ቀን 2015 ዓ.ም መከናወኑ ይታወሳል፡፡

   ይህንኑ ዝግጅት የአሜሪካን ድምጽ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል በደረጀ ደስታ አዘጋጅነት በመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 3፡00 ሰዓት ዜና በንግድና ምጣኔ ሀብት ክፍለ ጊዜው የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካን ተሳትፎ በማጉላት በሰፊው ዘገባውን አቅርቦታል፡፡  ከአሜሪካን ድምጽ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል የተወሰደውን ዝርዝር ዜና አብሮ በተያያዘው ቪዲዮ እና በቀጣይም ድርጅታችንን የሚመለከተውን ዋና ዝግጅት እንዲመለከቱ እንጋብዛለን፡፡

ጥራት መለያችን ነው!!

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

 376 total views,  3 views today

ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን መሳተፍ

ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን መሳተፍ

በአሜሪካን ሀገር ዋሽግንተን ዲሲ በሚገኘው የአሜሪካ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ዘርፍ ማህበራት ንግድ ምክር ቤት፤በኢትዮ-ፕሮሞሽን ኤል.ኤል.ሲ ከሄሌዝ ኤቨንትስ ጋር በጋራ በመተባበር የተዘጋጀውና እ.ኤ.አ ከሴፕቴምበር 24-25/2022 ለሁለት ቀናት የሚቆየው ዓለም አቀፍ የምግብ፤የመጠጥና የባህል ፌስቲቫል መካሔድ ጀምሯል፡፡

 በዚሁ ዝግጅት ላይ በድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ የሚመራ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም የማርኬቲንግ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ግሩም መሥፍንን ያከተተ ቡድን የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ አዲሱን ብላክ ዲር ዊስኪን ጨምሮ ተወዳጅ ምርቶቻችንን እያስተዋወቀ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡ በፌስቲቫሉ ላይ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና ተቀማጭነታቸውን አሜሪካን ሀገር ያደረጉ የተለያዩ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ጥራት መለያችን ነው!!

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

 324 total views,  2 views today

አስደሳች ዜና

THE BIZZ AWARDS

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆነውና 15 ዓመታት በላይ የድርጅቶችን አፈጻጸም በተለያየ መለኪያዎች በመመዘን እውቅና በመስጠት በሚታወቀውና 130 ዓለም ሀገራት በመስራት ላይ በሚገኘው እንዲሁም 3500 በላይ ታዋቂ አለም አቀፍ አምራች ድርጅቶች አባል ባሉት WORLD CONFIDERATION OF BUSINESSES, A winner of the most important business excellence award in the world, THE BIZZ AWARDS አሸናፊ መሆኑን ለድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ በድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጄሱስ ሞራን .. ነሐሴ 29/2022 በፃፈው ደብዳቤ በማሳወቁ የተሰማንን ከፍተኛ ደስታ እየገለጽን ይህም የድርጅታችን ሥራ አመራር ቦርድ፤ሥራ አመራርና የመላው ሠራተኛ ጠንካራ አመራር እና ቅንጅት ውጤት ነው፡፡


ይህ ውጤት የተገኘው ድርጅታችን በሥራ አመራር ጥራት ፤የተቀናጀ የአሰራር ሥርዓቶች ትግበራ፤በምርት ጥራት እንዲሁም በትርፋማነትና ውጤማነት ውስጥ ባሉ ዝርዝር መስፈርቶች መሰረት ያለበት የአፈፃፀም ደረጃ ተለክቶ የተገኘ በመሆኑ አሁንም በድጋሚ እንኳን ደስ አለን እያልን በቀጣይም ድርጅታችንን ከዚህ የበለጠ አፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደምናደርሰው ያለንን ሙሉ እምነት እንገልፃለን፡፡

ጥራት መለያችን ነው!!!

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

 362 total views,  3 views today

ማህበራዊ ኃሊፊነትን የመወጣት ተግባር!!

ማህበራዊ ኃሊፊነትን የመወጣት ተግባር!!

ብሔራዊ አሌኮሌና አረቄ ፋብሪካ በሰበታ ከተማ ቀበላ 07 ከስድስት ነጥብ ስድስት ሚሉዮን ብር በሊይ ወጪ በማድረግ አካባቢው ማህረሰብ ያስገነባቸውን አሥራ አምስት ሼዶች አጠናቅቆ የሰበታ ከተማ ከንቲባ ክብርት / ዓሌፊያ አብድርሃማን፤ክቡር አቶ ቶልሳ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክሌሊዊ መንግሥት የገንዘብና ኢኮኖሚ ሌማት ቢሮ ኃሊፊ እና የብሔራዊ አሌኮሌና አረቄ ፋብሪካ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፤ክቡር አቶ ሐብታሙ ሃይ ሚካዔሌ የመንግስት ሌማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዲ ዋና ዲይሬክተር፤ጥሪ የተረገሊቸው የመንግስት ሥራ ኃሊፊዎች፤የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ እና ሥራ አመራር አባሊት እንዱሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት ሚያዚያ 4 ቀን 2014 . አስመርቆ የሼዶቹን ቁሌፍ ሰበታ ከተማ ከንቲባ ክብርት / ዓሌፊያ አብድርሃማን አስረክቧሌ፡፡

 

 የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ የብሔራዊ አሌኮሌና አረቄ ፋብሪካ በአሌኮሌ መጠጡ ኢንደስትሪ የሚገኝ አንጋፋ የመንግሥት ሌማት ድርጅት መሆኑን ገሌፀው ድርጅታችን በአገር አቀፍ ረጃ ገበታ ሀገር፤ሸገር ማስዋብ፤ታሊቁ ህዲሴ ግድባችን ሀገር መከሊከያ ሠራዊት፤ተፈናቃ ወገኖቻችን፤ መካኒሳ አካባቢ ነዋሪዎች የተረጉ እና በማዕድ ማጋራት አማካኝነት ረጋቸውን በርካታ ድጋፎች በምሳላነት በመጠቀስ የሼድ ግንባታ ሥራውን አጠናቅቆ ድርጅታችን በማስረከቡ የተሰማቸውን ስታ በመገሌጽ ሥራው በወቅቱና በጥራት እንዱጠናቀቅ ተሳተፉት አካሊት በሙለ ምስጋናቸውን አቅርበዋሌ፡፡ ጥራት ያችን ነው!! ብሔራዊ አሌኮሌና አረቄ ፋብሪካ!!

 519 total views,  2 views today

ማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባር!!

ማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባር!!

   ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከበቅሎ ቤት ሰፈር ተወላጆችና ከዳግም ትንሳዔ ወንድማማቾች ማህበር ጋር በመሆን በአዲስ መልክ የተገነባውን የ፶ አለቃ ቸርነት መንገሻ እና የወ/ሮ ሸዋዬ መኖሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት ፤የወረዳው አመራር ተወካዮች፤የብስራት ኤፍ.ኤም ራዲዮ ባለቤት አቶ መሰለ መንግስቱ፤የማህበሩ ተወካዮችና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት አስመርቆ ለወ/ሮ ሸዋዬ አስረክቧል፡፡

 በወቅቱም የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በአልኮል መጠጡ ኢንዱስትሪ የሚገኝ የመንግሥት ልማት ድርጅት መሆኑንና ያለውን አንጋፋነትና ብቁ ተወዳዳሪነት በአጭሩ ለታዳሚዎች አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም ድርጅታችን በአገር አቀፍ ደረጃ ለገበታ ለሀገር፤ለሸገር ማስዋብ፤ለታላቁ ህዳሴ ግድባችን ፤ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እና በማዕድ ማጋራት አማካኝነት ያደረጋቸውን በርካታ ድጋፎች ለአብነት ከመጠቀሳቸውም በላይ ለመካኒሳ አካባቢ ነዋሪዎች የተደረጉ የኮሚኒቲ ፖሊሲንግ ጽ/ቤት እና የኮብል ስቶን መንገድ ግንባታዎችን በተጨማሪ በምሳሌነት በመግለጽ ይህ ሥራም የማህበራዊ ኃላፊነት ተግባር ዋነኛ አካል መሆኑን በመጥቀስ ወ/ሮ ሸዋዬን እንኳን ደስ አለዎት በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የድርጅታችን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ በበኩላቸው ሥራው የፈጠራባቸውን ደስታ በመግለጽ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ መሰል የማህበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን ማከናወኑን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጥቀስ የቤቱን ካርታ ለወ/ሮ ሸዋዬ በማስረከብ የእንኳን ደስ አለዎት በማለት መልዕክታቸውን በተጨማሪ አስተላልፈዋል፡፡

በዚህም ወቅት ለመኖሪያ ቤቱ ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረጉ ድርጅቶችና የማህበሩ አባላት የዕውቅና ሰርተፍኬት የተበረከተላቸው ሲሆን የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ እና ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም አቶ ተረፈ ሶርሱ ይገኙበታል፡፡

ጥራት መለያችን ነው!!!

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

 487 total views,  3 views today

የማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባር!!!

የማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባር!!!

 

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት አጠገባችን ለሚገኘው የመካኒሳ አካባቢ አንደኛ ደረጃ /ቤት የመማርማስተማር ሂደቱን የሚደግፉ አጠቃላይ ግምታቸው ከሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር በላይ የሆኑና ብዛታቸው ሁለት መቶ አርባ የፕላስቲክ ወንበሮች፤ስልሳ የፕላስቲክ ጠረጴዛዎች እንዲሁም በሦሰት ዙር የሚለገስ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ የንፅህና መጠበቂያ ሞዴሶች የድርጅታችን ከፍተኛ ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት በዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባት አማካኝነት ለት/ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር / ብሌን የካቲት 2/2014 . እንዲረከቡ ተደርጓል፡፡

 

በወቅቱም ድርጅታችን በተለይ የአካባቢያችን ማህበረሰብ በመደገፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚቀጥል በዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ የተገለፀ ሲሆን ድጋፉን የተረከቡት የት/ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር / ብሌን በት/ቤቱ ማህበረሰብ ሥም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

 

ጥራት መለያችን ነው!!

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

 649 total views,  2 views today

ዜና

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ምርቶቹ እንድትዝናኑ በአክብሮት ይጋብዛል!!!
ጥራት መለያችን ነው!!
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

 813 total views,  2 views today

ለአፍሪካ የሴቶች መረብ ኳስ ክለቦች ሻምፒዮ

በቱኒዚያ የሚካሄደው ለአፍሪካ የሴቶች መረብ ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ሀገራችንን እንዲወክሉ ከተመረጡት ክለቦች መካከል የሆነው የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የሴቶች መረብ ኳስ ቡድን ሚያዚያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ  ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ እና ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም የሥራ አመራር አባላት በተገኙበት የሽኝት  ሥነ ሥርዓት ተደርጎለታል::

መልካም ዕድል ለሴቶች መረብ ኳስ ቡድናችን!!!

 981 total views,  1 views today

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከክልል እና ከአዲስ አበባ ወኪሎች ጋር ያካሄደው ውይይት

ብሔራዊ  አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከክልል እና ከአዲስ አበባ ወኪሎች ጋር ያካሄደው ውይይት

የክልል ወኪሎች ስብሰባ

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከክልል ወኪሎች ጋር የውይይት መድረክ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በኤልገል ሆቴል አካሄደ፡፡ በዕለቱ የ2012 በጀት ዓመት አጠቃላይ የድርጅቱ የኦፕሬሽንና የፕሮጀክት አፈፃጸም የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ፣ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም የከፍተኛና መካከለኛ ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ በተጨማሪም የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት ዕቅድ አፈፃጸምና የቀጣይ ሁለተኛው 6 ወራት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

በ2012 በጀት ዓመትም የላቀ አፈፃጸም ላስመዘገቡ የኤክስፖርትና የሀገር ውስጥ ወኪሎች የእውቅናና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ በወቅቱም ድርጅታችንን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ አትራፊና ውጤታማ እንዲሆን ላደረጋችሁት ያላሰለሰ ጥረት የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን በማለት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወኪሎች ስብሰባ

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከአዲስ አበባ ወኪሎች እና ደንበኞች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ የካቲት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሆቴል አካሄደ፡፡ በዕለቱ የ2012 በጀት ዓመት አጠቃላይ የድርጅቱ የኦፕሬሽንና የፕሮጀክት አፈፃጸም የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ፣ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም የከፍተኛ ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ በተጨማሪም የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት ዕቅድ አፈፃጸምና የቀጣይ ሁለተኛው 6 ወራት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

በ2012 በጀት ዓመት ድርጅታችን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ አትራፊና ውጤታማ እንዲሆን ላደረጋችሁት ያላሰለሰ ጥረት የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን በማለት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ ገልጸዋል፡፡

አሁንም ትልቅ እውቅና ለድርጅታችን የተከበሩ ወኪሎቻችን

 1,569 total views,  1 views today

Contact Us

Mexico Square Behind Addis Ababa Technical College & Mekanissa
info@nalf.com.et, national.alcohol@gmail.com
+251 115 516 999 / +251 115 516 190
+251 115 513 299

Our Location