ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ምርቶቹ እንድትዝናኑ በአክብሮት ይጋብዛል!!!
ጥራት መለያችን ነው!!
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
913 total views, 2 views today
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ምርቶቹ እንድትዝናኑ በአክብሮት ይጋብዛል!!!
ጥራት መለያችን ነው!!
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
913 total views, 2 views today
አዲሱ ብሔራዊ ብላክ ዲር ዊስኪ ምርታችን ታዋቂ ደንበኞቻችን እና ወኪሎቻችን በተገኙበት በደርጅታች ዋና መስሪያ ቤት ነሐሴ 20/2013 ዓ.ም ከተዘጋጀ ፕሮግራም በኋላ በይፋ ወደ ገበያ መግባቱና በጥራቱም ተወዳጅነትን እያገኘ መጥቷል፡፡
ቅዳሜ መስከረም 29/2014 ዓ.ም ከጧቱ 4፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ቱሪስ ንግድ ሥራ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የብሔራዊ ብላክ ዲር ዊስኪ የማስተዋወቅ ሥራ በተሳካ ሁኔታ የተናወነ ሲሆን በወቅቱም የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር እንግዶች ጥራቱንና ደረጃውን በተመለከተ ለሰጣችሁን አዎንታዊ አስተያየት ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
ጥራት መለያችን ነው!!
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
862 total views, 2 views today
በቱኒዚያ የሚካሄደው ለአፍሪካ የሴቶች መረብ ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ሀገራችንን እንዲወክሉ ከተመረጡት ክለቦች መካከል የሆነው የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የሴቶች መረብ ኳስ ቡድን ሚያዚያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ እና ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም የሥራ አመራር አባላት በተገኙበት የሽኝት ሥነ ሥርዓት ተደርጎለታል::
መልካም ዕድል ለሴቶች መረብ ኳስ ቡድናችን!!!
1,081 total views, 2 views today
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከክልል እና ከአዲስ አበባ ወኪሎች ጋር ያካሄደው ውይይት
የክልል ወኪሎች ስብሰባ
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከክልል ወኪሎች ጋር የውይይት መድረክ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በኤልገል ሆቴል አካሄደ፡፡ በዕለቱ የ2012 በጀት ዓመት አጠቃላይ የድርጅቱ የኦፕሬሽንና የፕሮጀክት አፈፃጸም የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ፣ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም የከፍተኛና መካከለኛ ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ በተጨማሪም የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት ዕቅድ አፈፃጸምና የቀጣይ ሁለተኛው 6 ወራት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቧል፡፡
በ2012 በጀት ዓመትም የላቀ አፈፃጸም ላስመዘገቡ የኤክስፖርትና የሀገር ውስጥ ወኪሎች የእውቅናና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ በወቅቱም ድርጅታችንን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ አትራፊና ውጤታማ እንዲሆን ላደረጋችሁት ያላሰለሰ ጥረት የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን በማለት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ወኪሎች ስብሰባ
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከአዲስ አበባ ወኪሎች እና ደንበኞች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ የካቲት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሆቴል አካሄደ፡፡ በዕለቱ የ2012 በጀት ዓመት አጠቃላይ የድርጅቱ የኦፕሬሽንና የፕሮጀክት አፈፃጸም የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ፣ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም የከፍተኛ ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ በተጨማሪም የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት ዕቅድ አፈፃጸምና የቀጣይ ሁለተኛው 6 ወራት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቧል፡፡
በ2012 በጀት ዓመት ድርጅታችን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ አትራፊና ውጤታማ እንዲሆን ላደረጋችሁት ያላሰለሰ ጥረት የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን በማለት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ ገልጸዋል፡፡
አሁንም ትልቅ እውቅና ለድርጅታችን የተከበሩ ወኪሎቻችን
1,632 total views, 2 views today
የገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀው ባለ 12 ነጥብ መመዘኛ ተለክተው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 200 ከፍተኛ ግብር ከፋዮች መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተሰናዳ መርሐ ግብር ላይ የዕውቅና የዋንጫ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ድርጅታችን የተቀመጡትን መስፈርቶች ሁሉ በማሟላት ከልማት ድርጅቶች እንዲሁም ከሌሎች የቢዝነስ ተቋማት ጋር በመወዳደር የወርቅ ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን በመብቃቱ ደስ ብሎናል፡፡
በመሆኑም በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ ድርጅታችን የወርቅ ደረጃ ዋንጫ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እጅ ዋና ሥ/አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መስፍን አባተ ተረክበዋል፡፡ በዚህም የተሰማንን ከፍተኛ የደስታ ስሜት እየገለፅን ለቀጣይ ዓመታትም ይህንኑ በማስቀጠል ድርጅታችንን የምናስጠራበት እና ከአጋሮቻችን ጋር በመተባበር የበለጠ ለመሥራት እንደምንችል በሙሉ ልብ በመተማመን ነው፡፡
2,421 total views, 3 views today
መጋቢት 24፣ 2012
የኢትዮጵያ ብሄራዊ አልኮል እና አረቄ ፋብሪካ የተያዘው ሳምንት ሳያልቅ የንፅሕና መጠበቂያ አልኮል እና ሳኒታይዘር ማምረት እጀምራለሁ አለ፡፡
ፋብሪካው የዓለም የጤና ድርጅት WHO ያስቀመጠውን መስፈርት ተከትሎ በቀን 5 ሺ ሊትር ሳኒታይዘር ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑን ለሸገር ነግሯል፡፡
1,424 total views, 2 views today
Contact Us
Our Location