National Alcohol & Liquor Factory

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከክልል እና ከአዲስ አበባ ወኪሎች ጋር ያካሄደው ውይይት

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከክልል እና ከአዲስ አበባ ወኪሎች ጋር ያካሄደው ውይይት

ብሔራዊ  አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከክልል እና ከአዲስ አበባ ወኪሎች ጋር ያካሄደው ውይይት

የክልል ወኪሎች ስብሰባ

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከክልል ወኪሎች ጋር የውይይት መድረክ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በኤልገል ሆቴል አካሄደ፡፡ በዕለቱ የ2012 በጀት ዓመት አጠቃላይ የድርጅቱ የኦፕሬሽንና የፕሮጀክት አፈፃጸም የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ፣ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም የከፍተኛና መካከለኛ ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ በተጨማሪም የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት ዕቅድ አፈፃጸምና የቀጣይ ሁለተኛው 6 ወራት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

በ2012 በጀት ዓመትም የላቀ አፈፃጸም ላስመዘገቡ የኤክስፖርትና የሀገር ውስጥ ወኪሎች የእውቅናና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ በወቅቱም ድርጅታችንን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ አትራፊና ውጤታማ እንዲሆን ላደረጋችሁት ያላሰለሰ ጥረት የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን በማለት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወኪሎች ስብሰባ

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከአዲስ አበባ ወኪሎች እና ደንበኞች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ የካቲት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሆቴል አካሄደ፡፡ በዕለቱ የ2012 በጀት ዓመት አጠቃላይ የድርጅቱ የኦፕሬሽንና የፕሮጀክት አፈፃጸም የድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ፣ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከቤ ቁምቢ እንዲሁም የከፍተኛ ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ በተጨማሪም የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት ዕቅድ አፈፃጸምና የቀጣይ ሁለተኛው 6 ወራት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

በ2012 በጀት ዓመት ድርጅታችን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ አትራፊና ውጤታማ እንዲሆን ላደረጋችሁት ያላሰለሰ ጥረት የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን በማለት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ ገልጸዋል፡፡

አሁንም ትልቅ እውቅና ለድርጅታችን የተከበሩ ወኪሎቻችን

 1,632 total views,  2 views today

Contact Us

Mexico Square Behind Addis Ababa Technical College & Mekanissa
info@nalf.com.et, national.alcohol@gmail.com
+251 115 516 999 / +251 115 516 190
+251 115 513 299

Our Location