ማዕድ ማጋራት !!!
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ማህበራዊ ኃላፊነት የመወጣት ተግባሩን እንደቀጠለ ሲሆን ከልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ለማዕድ ማጋራት ተግባር የሚውል እና በአስር ኪ.ግ የታሸገ ከአንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ብር ላይ የሚያወጣ አሥራ አምስት ኩንታል የስንዴ ዱቄት ጷጉሜ 01 ቀን 2015 ዓ.ም በድርጅታችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ እና ሥራ አመራር አባላት አማካኝነት ለጽ/ቤቱ ተወካዮች አስረክቧል፡፡
33 total views, 2 views today