National Alcohol & Liquor Factory

Year 2011 E.C

Year 2011 E.C

በብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ በርካታ ተግባራት ተከናውኗል፣

  • የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ሕፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት በድርጅቱ ለሚረዱ 500 ተማሪዎች የደብተርና የስክሪፕቶ ወጪ እንዲሸፍኑላቸው የብር 12,000 ድጋፍ ተሰቷል፡፡
  • ለኢትዮጵያ ሠራተኞች ኮንፌደሬሽን ለስፖርት ዝግጅት የ100,000 ብር በገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዲስ ለሚያስገነባው ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ የ100,000 ብር በገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡
  • ለሰበታ ፖሊስ ጣቢያ ግንባታ የ25,000 ብር በገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የመፈናቀል ችግር ምክንያት ተፈናቃዮችን ለመርዳት ገቢ እያሰባሰበ ያለ በመሆኑ በፋብሪካችን ለዚህ ዓላማ የሚውል የ20,000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • ልደታ ክፍለ ከተማ ወላጆቻቸውን በኤች.አይ ቪ/ኤድስ ላጡ 5 ህፃናት ድርጅታችን ተረክቦ በየወሩ ቋሚ ድጋፍ የሚያደርግላቸው ሲሆን እንዲሁም ለበዓል መዋያና ለትምህርት ቁሳቁስ ጨምሮ በዓመቱ 56,000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከአፀደ ህፃናት እስከ 4ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ከፍለው መማር ለማይችሉ ህፃናትን ለማስተማር እያስገነቡት ላላው የህንፃ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ እንድናደርግላቸው በጠየቁት መሠረት 16,000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • የኦሮሚያ ክልል ሴቶች ፌዴሪሽን በጋራ እንደግፍ ተጓዥ አገር አቀፍ ንግድ ትርኢትና ባዛር ገቢ ማሰባሰቢያ ድርጅታችን የስፖንሰር ድጋፍ እንድናደርግ በጠየቁት መሰረት የብር 20,000 ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • የኦሮሚያ ልማት ማህበር ቶምቦላ ሎተሪ በመግዛት ድጋፍ እንድናደርግላቸው በጠየቁን መሰረት የአንድ ሎተሪ ዋጋ በቁጥር 1000 ሎተሪ በመግዛት ለሰራተኞች እንዲሰጥ የብር 25,000 ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች ማቋቋሚያ በተጠየቀው ድጋፍ መሰረት የብር 150,000.00 ድጋፍ ተደርጓል
  • ድርጅታችን አዲስ አበባ (ሸገር)ን ለማስዋብ ለታቀደው ፕሮጀክት የ5,000,000.00 ብር፣
  • ለተለያዩ ሕዝባዊና በጎ አድራጎት ማኅበራት የብር 71,100 ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ የብር 5,595,100 ድጋፍ ተደርጓል፡፡

 1,853 total views,  3 views today

Contact Us

Mexico Square Behind Addis Ababa Technical College & Mekanissa
info@nalf.com.et, national.alcohol@gmail.com
+251 115 516 999 / +251 115 516 190
+251 115 513 299

Our Location