National Alcohol & Liquor Factory

Year 2012 E.C

Year 2012 E.C

የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በልደታ ክፍለ ከተማ ለወረዳ 10 አካባቢ ለሚገኙ 46 አባወራዎች በሁለት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ብር ያሰራውን ዘመናዊ መፀዳጃና መታጠቢያ ቤት አጠናቅቆ ለነዋሪዎቹ አስረከበ፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን አባተ በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በሀገራችን አልኮል መጠጥ አምራች ኢንዱስትሪ ውስጥ አንጋፋ፤ዘመናዊና ከፍተኛ የማምረት አቅም ያለው የመንግሥት ልማት ድርጅት መሆኑን ጠቅሰው የአልኮል መጠጥ ምርት ዋና ግብዓት የሆነውን ንፁህ አልኮልን ጨምሮ የተለያዩ አልኮል መጠጦችን እና እሳት አልኮል በከፍተኛ ጥራት በተፈለገው መጠን አምርቶ ለደንበኞቹ በማቅረብ  የሚታወቅ አትራፊ የመንግሥት ልማት ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የእሳት አልኮል ምርትን ለገበያ ከማቅረብ ባሻገር  የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በአዲስ መልክ አምርቶ ለገበያ ማዋሉን ገልፀዋል፡፡ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በፕሮጀክት አፈፃፀም ብቃት እንዳለው እና ይህም ዛሬ ተጠናቅቆ ለርክክብ የበቃው  ሥራ አንዱ ማስረጃ መሆኑን በምረቃው ወቅት አብራርተዋል፡፡ የማህረሰቡን ችግር የሚፈቱ ተመሳሳይ ሥራዎች በቀጣይነት እንደሚሰሩ ቃል ገብተው የተሰራውን መታጠቢያና መፀዳጃ ቤት በእንክብካቤ መያዝ ላይ ህብረተሰቡ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ድርጅታችን የማህበራዊ ኃላፊነቱን በተገቢው ሁኔታ እየተወጣ ያለ ድርጀት ሲሆን ለዚሁ ዓላማ ከፍተኛ በጀት በየዓመቱ በመመደብ የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፋብሪካው የመኖሪያ አካባቢያቸው ምቹ ያልሆነና ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አብራርተዋል፡፡

በዚህም መሰረት በልደታ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 አካባቢ የሚኖሩ 46 አባወራዎች ከረጅም ዓመታት በፊት በበጎ አድራጎት ድርጅት የተሰራላቸው መፀዳጃ ቤት ከአገልግሎት ውጪ በመሆኑ ድጋፍ እንዲደርግላቸው በጠየቁት መሰረት የድርጅቱ ሥራ አመራር ተመልክቶ ለፕሮጅክቱ ከ236 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ እና በዘመናዊ መልክ ሰርቶ በማጠናቀቅ ሚያዝያ 20 ቀን 2012 ዓ.ም የወረዳ 10 አስተዳደር ኃላፊዎች በተገኙበት አስመርቆ ለአካባቢው ነዋሪዎች አስረክቧል፡፡

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ተፈሪ መርዲሳ በበኩላቸው የተጠቀሱትን አባወራዎች ችግር ድርጅቱ ተመልክቶና ካለው ውሱን በጀት ቀንሶ በመመደብ ይህንን ጥራቱን የተበቀ መታጠቢያና መፀዳጃ ቤት ገንብቶ በማስረከቡ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ በወረዳው አስተዳዳር ስም ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም መሰል የመንግስት ልማት ድርጅቶችንና ባለሀብቶችን በማስተባበር የማህረሰቡን ችግር ፈቺ  የሆኑ ተመሳሳይ ሥራዎች በቀጣይ መሰራት እንዳለባቸውና ወረዳውም ለዚህ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

የወረዳ 10 አካባቢ ነዋሪ የሆኑት እና የመፀዳጃ ቤቱ ሥራ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ተክለሚካዔል ታደሰ በበኩላቸው ከረጅም ዓመታት በፊት ተሰርቶ በአሳዛኝ ሁኔታ አገልግሎት መስጠት ያልቻለውን መፀዳጃ ቤት በአዲስ መልክ ለማሰራት ድጋፍ ለማግኘት ያልሄዱበት ድርጅትና ያላንኳኩት ቢሮዎች እንዳልነበሩ ገልፀው ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ግን በአጭር ጊዜ ይህንን የመሰለ ጥራቱን የጠበቀ መታጠቢያና መፀዳጃ ቤት ሰርቶ በማስረከቡ የተሰማቸውን ደስታ የሚገልፁበት ቃል እንደሚያጥራቸውና ይህም ከድርጅቱ ሠራተኞች ጀምሮ እሰከ ከፍተኛ ኃላፊዎች ያላቸውን ትጋትና ቀናነት እንደሚያሳይ ከዚህም ሌሎች ድርጅቶች ሊማሩበት እንደሚገባ ያላቸውን ሃሳብ ገልፀዋል፡፡

 261 total views,  1 views today

Contact Us

Mexico Square Behind Addis Ababa Technical College & Mekanissa
info@nalf.com.et, national.alcohol@gmail.com
+251 115 516 999 / +251 115 516 190
+251 115 513 299

Our Location