በ2013 በጀት ዓመት የተደረጉ ዋና ዋና ማህበራዊ ድጋፎች
- በልደታ ክፍለ ከተማ 5፣ በላፍቶ ክ/ከተማ 5 እና በሰበታ 5 በጠቅላላው ለ15 ወላጆቻቸውን በኤች.አይ ቪ/ኤድስ ላጡ ህፃናት በየወሩ ለእያንዳንዳቸው የ600 ብር ፣ የዘመን መለወጫ፣ ለገና እና ለፋሲካ በዓል ለእያንዳንዳቸው 3000 ብር እና የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ ለእያንዳንዳቸው 1,000 ብር በጠቅላላ በድምሩ የ168,000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- ለመቄዶንያ አረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን ከድርጅታችን ሠራተኞች 125,345 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- በሀገራችን ከሰኔ 23/2012 ጀምሮ በተነሳው አለመረጋጋት የንብረት ጉዳት ለደረሰባቸው 4 የድርጅታችን ወኪሎች በጠቅላላው 630 ሳጥን መጠጥ ከነሳጥኑ ወደ ብር ሲቀየር 1,004,878 ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- በችግር ላይ ለሚገኙ 88 የድርጅቱ ጡረተኞች 286,664.00 ብር የሚያወጣ የምግብ ቁሳቁስና ልዩ ልዩ ስጦታዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- በስቴዲዬም አካባቢ ለሚኖሩ 300 የጎዳና ተዳዳሪዎች ለ10 ቀን የምሳና የእራት ምገባ የሚሆን 270,000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- በሀገር አቀፍ ደረጃ ጉዳት ለደረሰባቸው ማቋቋሚያ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በኩል 1,000,000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የ1,000,000 ብር ቦንድ በመግዛት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እንድናደርግ በቀረበው ሀገራዊ ጥሪ መሰረት በን/ስ/ላ ክ/ከተማ እና በልደታ ክ/ከተማ በኩል በአጠቃላይ የ1,000,000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም በዓይነት 80,000 ብር የዋጋ ግምት ያለው ለሳኒታይዘርነት አገልግሎት የሚውል 1,000 ሊትር የእሳት አልኮል ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- ለቀይ መስቀል 100,000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- በሀገር አቀፍ ደረጃ በሦስት ቦታዎች ለሚሰሩ ፓርኮች መንግስት ባቀረበው የድጋፍ ጥሪ መሰረት ብር 10 ሚሊዮን ለመክፈል ቃል በተገባው መሰረት ተከፍሏል፡፡
- ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለይም በቤንሻንጉል ክልል በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚሆን 50,000 ብር በጥሬ ገንዘብ እና 796 ባለ 250 ሲሲ ሳኒታይዘር በዓይነት ወደ ብር ሲቀየር 51,740 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- ለአማራ ባህል ማዕከል ግንባታ ብር 50,000 ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- ለልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ለህብረተሰቡ የመጸዳጃ ቤት፣የመታጠቢያ ቤት እና ከ120 ሜትር በላይ የፈሳሽ ማስወገጃ መስመር ግንባታ 343,492 ብር ወጪ ተደርጎ ግንባታ ተፈጽሟል፡፡
- ለበለስ ስኳር ፋብሪካ ምረቃ በዓል ለስኳር ኮርፖሬሽን 500,000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
- ለተለያዩ ሕዝባዊና ማህበራት 42,950 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም
- ለኮቪድ 19 መከላከያ የሚሆን ለተለያዩ ሕዝባዊና ማህበራት 230,475 ብር የሚያወጣ የሳኒታይዘር እና የእሳት አልኮል ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ በብር እና በአይነት 16,303,544 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
1,075 total views, 2 views today